Woreda Three Prosperity Party Office

What's Hot

በባለፉት ስድስት ወራት 27,509 ፀጋዮችን በመለየት ለ19,112 ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ገልጿል።

Table of Content

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማና ከአስሩም ወረዳዎች ከመጡ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን አፈፃፀሙን ገምግሟል።

በዚህም በነበረው የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም 27,509 ፀጋዎችን በመለየት ለ19,112 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ለ70,360 ወጣቶችና ሴቶች በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱ፣በስራ እድል ፈላጊ ወጣቶች ምዝገባ ከ25ሺ በላይ መመዝገቡ፣ለ20,242 ወጣቶችና ሴቶች የልል ስልጠና መስጠቱ፣ከምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች፣ከብድር ስርጭትና ማስመለስ አንፃር የተሠሩ ስራዎች በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም በበጎ ፍቃድ፣በሪፎርም፣አገልግሎትን ከማዘመን፣የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግና ተጠያቂነትን ከማስፈን አንፃር የተሠሩ ተግባራት በስፋት ቀርበዋል።

መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ የስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት ቁልፍ ተግባር መሆኑን በማንሳት በቀሪ ጊዜያት ያሉ ዕቅድን ለማሳካት ፀጋዎችን አሟጦ መጠቀም ፣ ተግባራትን መገምገምና በውጤት ማጀብ ፣ አመራሩን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ማስገባትና የተጠያቂነት ስርዓትን ማስፈን ፣ ተግባራትን ወጥ በሆነ መልኩ አስተሳስሮ መምራት ፣ ስራዎችን መሬት አስነክቶ መምራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል የስራ እና ክህሎት ሜክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ በበኩላቸው የ2ኛ ሩብ ዓመት የስራ ዕድል ፈጠራ ከሚፈለገው አኳያ ቀሪ ስራዎች ያሉ በመሆኑ የተግባሩን ክብደት በመረዳት መደበኛ ስራዎችን ከንቅናቄ ስራዎች ጋር አስተሳስሮ መስራት ፣ ተልዕኮ ተቀብሎ መፈፀም፣ ግምገማዎችን ወደ ውጤት መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም በነበረው የስድስት ወር አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።

admin

danieltesfahun1993@gmail.com https://lkworedathreepp.org

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

Trending News

Editor's Picks

በባለፉት ስድስት ወራት 27,509 ፀጋዮችን በመለየት ለ19,112 ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማና ከአስሩም ወረዳዎች ከመጡ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን አፈፃፀሙን ገምግሟል። በዚህም በነበረው የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም 27,509 ፀጋዎችን በመለየት ለ19,112 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ለ70,360 ወጣቶችና ሴቶች በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱ፣በስራ እድል ፈላጊ...

የክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሀዘን መግለጫ !!!

ታዋቂው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል። ለአርቲስት ነጻነት ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና አድናቂዎች በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ። ፈጣሪ ነብሱን በአጸደ ገነት ያኑር። Artistiin beekamaan Natsaannat Warqinah dhibee tasaa isa muudateen addunyaa kanarraa du’aan boqachachuu isaatiin gaddi guddaan natti dhagahameera. Maatii artistii Natsaannatiif, jaalattootaa fi dinqisiifattootasaa hundaaf jajjabina hawwa. Waaqayyoon...

Bazaars Strengthen Market Linkages Between Producers and Consumers

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ የንግድ ጽ/ቤት፣ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት፣ የህብረት ስራ ጽ/ቤት፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤትና የኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን መጪውን የገና በዓል ምክኒያት በማድረግ የንግድና ባዛር በወረዳ 14 አስተዳደር በየካ አባዶ መስቀለኛ አደባባይ በይፋ ተከፍቷል ።

የጥምቀት በዓል አከባበርን በማስመልከት የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮችና የወረዳው አጠቃላይ አመራር በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሄደ።

In Africa, regional blocs are focusing on economic integration and collective security, aiming to present a unified voice in global negotiations. Meanwhile, debates over trade, climate commitments, and digital governance dominate international summits, reflecting the interconnected nature of modern politics.

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፥ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው።

Must Read

©2026- All Right Reserved. Designed and Developed by Woreda Three Prosperity Party Office.