Woreda Three Prosperity Party Office

What's Hot

About Us

የለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

ይህ ክፍል ተጠቃሚዎች የቦታ መረጃን በቀላሉ ለማሳየት እና ለመዳረሻ የሚያገለግል ዋነኛ መስክ ነው፤ ዋነኛ ተግባሩም የድርጅቱን አድራሻ፣ አገልግሎት ቦታዎች እና አስፈላጊ መረጃዎችን በግልጽ መልኩ ማቅረብ ሲሆን ተጠቃሚዎች ቦታውን በቀጥታ ለማግኘት እና ለማስታወቂያ መረጃ ማየት ይችላሉ።

Lemi-kura Woreda 3, Addis Ababa, Ethiopia

lemikuraworedathee@lemikurapp.org

+2519-20-66-97-21

ዋነኛ ዓላማ እና ኅብረ ብሔራዊነት

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው። ፓርቲያችን ኅብረ ብሔራዊነት በሁሉን አቀፍነት፣ በብዝኃ ልሳንነት እና በአሳታፊነት ሊገለጽ ይገባል ብሎ ያምናል።

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና የማኅበረሰብ እሴት

ህብረ ብሔራዊ አንድነት ብዝኃነትን እንደጸጋ የሚመለከት ሲሆን ለሁሉም ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕውቅና የሚሰጥ ነው። ከታሪክ ትሥሥር፣ አሁናዊ ሁኔታና የጋራ ጥቅም በመነሳት ጠንካራ ኅብረትና ትብብር ሊኖራቸው ይገባል የሚል ዕሴት ነው። አንድነት ማንነታችን እርስ በርሱ የተጋመደ፣ የተሠናሰለ እና የተዋሐደ መሆኑን አመላካች ነው። ይህ አመለካከት ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን መቆም፣ መሥራት፣ መደጋገፍ እና መተጋገዝ እንደሚገባን ያሳያል።

ታሪክ፣ ትምህርት እና የወደፊት ትኩረት

ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ታሪካዊና ነባራዊ በደሎችን ከማድበስበስ ይልቅ ታርመው እንዲሄዱ ይመርጣል። ይህም ወዳጅነትን ለማጠናከር የሚያደርግ አካሄድ ነው። ከሚከፋፍሉ ትርክቶች ይልቅ እውነታዎችን በማጉላት፣ ከትናንት ትምህርቶችን በመውሰድ እና ዛሬና ነገ ላይ በማተኮር እህታማማችነትና ወንድማማችነት ማጠናከርን ይመርጣል። በብዝኃነታችን ደምቀን በአንድነታችን በርትተን ወደፊት የምንራመድበት የውበትና የጥንካሬ ምንጭ ነው። ፓርቲያችን “በኅብረት ሆነን እንበለጽጋለን፤ በልጽገንም በኅብረት እንኖራለን” በሚል መርሕ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው።

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፥ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው።

Must Read

©2026- All Right Reserved. Designed and Developed by Woreda Three Prosperity Party Office.