Woreda Three Prosperity Party Office

What's Hot

Lemi Kura Sub‑City Woreda 03 Prosperity Party Branch Office

“We, the members of the Prosperity Party Committee of Lemi Kura Sub‑City Woreda 03, recognizing that our country Ethiopia is a multinational state built upon shared values and a common vision embraced by its nations, nationalities, peoples, and diverse identities, commit ourselves to work diligently. For our sub‑city, for our city, and for our country as a whole, we strive to establish a peaceful, democratic, just, and inclusive political, economic, and social order. We pledge to carry out our collective and organizational mission with competence and dedication.”

Mr. Tamrat Ermias Albamo

Lemi Kura Sub‑City Woreda 03 Prosperity Party Branch Office Head

መጋቢት 24 በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት፡፡ ትናንትን እና ዛሬን፤ ዛሬን እና ነገን፤ የዳርና የመሐልን፤ ግንባር እና አጋርን፤ አርሶ እና አርብቶ አደርን፣ ግለሰብና ቡድንን፣ አካቢያዊ እና ሀገራዊ ማንነትን፣ በመደመር ዕሳቤ ያግባባች ቀን ናት፡፡ 

ከዕዳ ወደ ምንዳ ለመጓዝ መነሻ ሆናለች፡፡ ለመፍጠርና ለመፍጠን የሚያስችል ዐውድ ዘርግታለች፡፡ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ አማካኝነት ሀገር የሚቀይሩ ፕሮጀክቶች ተጀምረው እንዲጨረሱ፤ ተጠናቅቀው እንዲመረቁ አስችላለች፡፡ እንደ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ሀገራዊ ሐሳቦች ከዕንቅፋት ተርፈው ለብርሃን እንዲበቁ አድርጋለች፡፡ 

በይቅርታ እንሻገር፣ በፍቅር እንደመር፤ ጽዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያ፤ አረንጓዴ ዐሻራ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ፤ የሌማት ትሩፋት፣ የምግብ ሉዓላዊነት፤ የትምህርት ቤት ምገባ፤ የኮሪደር ልማት፤ ወዘተ. ተነሣሽነቶች የመጋቢት 24 ውጤቶች ናቸው፡፡
የትምህርት ሪፎርም፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም፤ የውጭ ግንኙነት ሪፎርም፤ የጸጥታ ተቋማት ሪፎርም፤ የፍትሕ ተቋማት ሪፎርም፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ሪፎርም፤ የሚዲያ ሪፎርም፤ ወዘተ… የመጋቢት 24 ፍሬዎች ናቸው፡፡ 

ኢትዮጵያ ውስጥ ትናንት እየራቀ፣ ነገ እየቀረበ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ተገቢዋን ቦታ ለመያዝ ተቃርባለች፡፡ በመደመር ጎዳና፣ ኢትዮጵያን ወደ ብልጽግና ለማድረስ የተጀመሩት ሥራዎች ሁሉ ፍሬያቸውን ማሳየት ጀምረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በድህነትና ኋላቀርነት ይነሳ የነበረው ስሟ በስንዴ፣ አረንጓዴ አሻራ፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ የቱሪስት መዳረሻ ምቹ ቦታዎች፣ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ወዘተ… በጎ ገፅታዎች መጠራት ጀምሯል። 

ዘርፈ ብዙ የመጋቢት 24 የለውጥ ፍሬዎችን መከባከብና ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ፍሬዎችን ከጃርቶች እና ከቀበሮዎች መጠበቅም አለብን፡፡ ማንም ከመዳረሻችን አያስቀረንም፡፡ ማንም እንዲያዘገየንም አንፈቅድም፡፡ በሚወረወሩብን ድንጋዮች ብልጽግናን እንገነባበታለን፡፡ የመጋቢት 24ን ፍሬዎች በየአንዳንዱ የኢትዮጵያ መንደሮች ለማድረስ ተግተን እንሰራለን፡፡

አቶ ኤርሚያስ ታምራት

የለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

የብልጽግና ፓርቲ መርሆዎች

  • ሕዝባዊነት
  • ዴሞክራሲያዊነት
  • የሕግ የበላይነት
  • ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት
  • ተግባራዊ እውነታ
  • ሀገራዊ አንድነትናኅብረብሔራዊነት

የብልጽግና ፓርቲ እሴቶች

  • ኅብረ ሀገራዊ አንድነት
  • የዜጎች ክብር
  • ፍትህ

የብልጽግና ፓርቲ አላማዎች

  • ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ቅቡልነት ያለው ፣ ዘላቂ ሀገረ መንግሥት መገንባት
  •  ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ  ሥርዓት መገንባት
  •  ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያሰፍን ማኅበራዊ ልማትን ማረጋገጥ
  • ሀገራዊ ክብርንና ጥቅምን ማዕከል ያደረገ የውጭ  ግንኙነት ማካሄድ

የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮ

  • ለሰዎች ፍላጎት ይግባኝ
  • ዴሞክራሲያዊነት
  • የህግ የበላይነት
  • ልማት እና እኩል ተጠቃሚነት
  • ሀገራዊ አንድነት እና ብሄርተኝነት

የብልጽግና ፓርቲ ራዕይ

የብልፅግና ፓርቲ ራዕይ በዋናነት “በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር የተረጋገጠ ብልፅግና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ማረጋገጥ” የሚል ነው። 
የፓርቲው ራዕይ እና የርዕዮተ-ዓለም ማዕቀፍ (መደመር) በስፋት እንደሚከተለው ይገለጻል፡-
  • የጋራ ብልፅግና፡ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ልማት የዳበረች፣ የዜጎቿ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት እና በአፍሪካ የምትታይ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን መገንባት።
  • መደመር (Synergy/Convergence)፡ ያለፉትን ጥፋቶች በማረም፣ አዳዲስ አመለካከቶችን በመያዝ፣ ተበታትኖ በመጥፋት ፋንታ ተሰባስቦና ተጣምሮ በአዲስ ጉልበት መነሣት።
  • ብሔራዊ አንድነትና ማንነት፡ ልዩነትን በአግባቡ በመያዝ ጠንካራ የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት መገንባት።
  • ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፡ ልማት በሰው ህይወት ላይ እሴት የሚጨምር “ሰው ተኮር” እንዲሆን ማድረግ።
  • የፓን-አፍሪካኒዝም መርሆች፡ የአፍሪካን አንድነት ማጠናከር እና ሀገራት በአለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነታቸው እንዲጨምር ማድረግ። 
በአጭሩ የብልፅግና ፓርቲ ራዕይ “የዜጎች ክብር የተከበረባት፣ ብልፅግናዋ የተረጋገጠባት ጠንካራ ኢትዮጵያ” መፍጠር ነው። 

የወረዳዉ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች

Mr. Tamrat Ermias Albamo

Branch Office Head

Mr. Chalchisa Beshana

የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ

Miss Fikrte Getaneh

የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ

አቶ ሳሙኤል በቀለ ነገሪ

የወጣት ክንፍ ዘርፍ ሀላፊ

ወ/ሮ ጌቴ በቀለ ደበሌ

የሴቶች ክንፍ ዘርፍ ሀላፊ

አቶ ተመስገን ቢተው ስዩም

Head of the Inspection and Ethics Commission

የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ

Mr. Chalchisa Beshana

የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ

ዋና ዋና ተግባራት

  • ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ፣ ቀጠናዊ፣ ሀገራዊና ከባቢያዊ ሁኔታዎችን ሳይንሳዊ በሆነ አግባቡ በመተንተን፣ ፈጣን ስትራቴጂያዊ ምላሽ በመተግበር ለብልፅግና ጉዞ ተገቢ ፖለቲካዊ ሁኔታ መፍጠር።

  • የብልፅግና አመራሩንና አባሉን በየጊዜው በፓርቲው እሳቤዎችና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ፣ እውቀታቸውንና የክህሎት አቅማቸውን በማሳደግ፣ አመራሩ አስተሳሰብና ተግባር እንድነት እንዲረጋገጥ መሥራት።

  • የአመራሩን፣ የአባሉንና የህዝቡን የዕርስ በርስ ግንኙት በማጠናከር፣ የመንግስታት ግንኙነትን እውን በማድረግ፣ የፌዴራል ሥርዓቱን ማጠናከር።

  • በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ የህዝብ ውይይት በማድረግ፣ በሁሉም መስክ የህዝብ ተሳትፎ እንዲጎለብትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በማነሳሳት፣ ህዝቡ በፓርቲው ላይ ያለውን ቅቡልነት ማሳደግ።

  • በፓርቲው የተነደፉ የልማት ኢኒሼቲቮችን በአግባቡ በመምራትና በማስተባበር፣ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ማድረግ።

  • በከተማችን መልካም አስተዳደር እውን እንዲሆንና የአገልግሎት አሠጣጥ እንዲሻሻል በማድረግ፣ የህዝብ ቅሬታን በመፍታት እርካታን ማሳደግ።

  • ደረጃውን የጠበቀና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቤተ-መፅሀፍትና ኢ-ላይብራሪ በብቃት በማደራጀት፣ የአባሉንና የአመራሩን አቅም ለመገንባት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር።

  • የአመራሩንና የአባሉን አቅም የሚያሳድጉ የተደራጁ ሥልጠናዎችን በመስጠት፣ የአስተሳሰብ አድማሳችንን ማስፋትና የፓርቲውን የመፈፀምና ማስፈፀም አቅም ማሳደግ።

  • በከተማችን ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎችና ፖለቲካዊ እና ድርጅታዊ ሥራዎች በማከናወን፣ የመማር ማስተማር ሥራ ጤናማና ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ።

የአደረጃጀት ዘርፍ

Miss Fikrte Getaneh

የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ

ዋና ዋና ተግባራት

  • የፓርቲው የአደረጃጀትና የአሰራሮችን በማዘመንና ተግባራዊ በማድረግ፣ የፓርቲውን ተቋማዊ ጥንካሬ ማረጋገጥ።

  • በግልፅ ተልዕኮ ላይ የተመሠረተ የምደባ ሥርዓት በመዘርጋትና የምዘናና እውቅና ሥርዓት እውን በማድረግ፣ የፓርቲ ተቋማዊ ጥንካሬ ማረጋገጥ የሚችሉ ጤታማ ተግባራትን ማከናወን።

  • በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና አሠራር መሰረት ነባሩን በማጥራት፣ አዳዲስ አባላት ምልመላ በማካሄድ፣ የፓርቲውን መሠረት የማስፋት ሥራ መሥራት።

  • የፓርቲውን የውስጠ-ፓርቲ ዴሞክራሲ የበለጠ ለማዳበር የሚያስችል ጤታማ ተግባራት ማከናወን።

  • የፓርቲውን የአመራር ሥርዓት ለማጠናከር፣ ግንባር ቀደም፣ ተኪና ኮር አመራር በየደረጃው ማፍራትና ማብቃት።

  • የተሟላ፣ የጠራና ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋትና በማዘመን፣ ጥቅም ላይ ማዋል።

  • ለአደረጃጀት የተሰጡ የ2018 ሀገራዊና ከተማዊ ምርጫ ተግባራት ማከናወን።

  • የአደረጃጀት ሥራዎች ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት።

  • ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር የሚያስችል ጤታማ ክትትልና የድጋፍ አሠራር ጥቅም ላይ ማዋል።

የወጣት ክንፍ ዘርፍ

Mr. Samuel Bekele Negeri

የወጣት ክንፍ ዘርፍ ሀላፊ

ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናት፤ በታሪክ ከተከብራ የኖረችው በወጣቶች ግንባር ቀደም መሪነትና ተሳትፎ ነው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ለውጡን ለመፍጠር ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ በለውጡ ሂደት በተመዘገቡ ድሎች ውስጥ የማይተካም ተጫውተናል።

በለውጡ ዘመን ሊጋችን በየደረጃውና በየዘርፉ፣ በተለይም በበጎ ፍቃድ ሥራ ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ያመነጯቸውን በርካታ የብልፅግና ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ እጅግ አመርቂር ብርብ አድርገናል።

እንደ ክፍለ ከተማችንም በርካታ ተግባራትን በስኬት አጠናቀናል።

ውድ የክፍለ ከተማችን ወጣቶች፣ ኢትዮጵያ ደምቃ የምናያት ግንባር ምኞት ሊሆን አይችልም።

በወጣቶች የምትሰራ የተሻለች ኢትዮጵያን ነገ ማየት ዛሬ አንድ ሆነን መቆም አለብን።

አንድ ሆነን መቆም የምንችለው በሊጋችን ግንባር ቀደም፣ ትግልና መሪነት ህብረታችንን የሚሸርብሩ ፅንፈኝነት፣ ዘረኝነት፣ ሌብነትን የመሰሉ ተሻጋሪ ህመሞችን ዛሬውኑ መታከምና መዳን ነው።

ለዚህ ወሳኝ ትግል እንትጋ።

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አላማዎች

  • የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም በወጣቱ ውስጥ ሰርፆና ተግባራዊ ሆኖ መላው የአገራችንን ወጣቶች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ።

  • ወጣቶች በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በየደረጃው ባለ የልማት የዲሞክራሲና የሰላም ግንባታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል።

  • ወጣቶች ህገ-መንግስቱ ያጎናፀፋቸውን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በትክክል ሥራ ላይ እንዲውሉ፣ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ለመብታቸው እንዲታገሉ ማስቻል።

  • የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የወጣቶችን አቅም በመገንባት፣ የወጣቶች እኩልነትን የሚገድቡ ባህላዊና ልማዲዊ ተጽዕኖዎችን በመለየት፣ በሀገር እድገትና በወጣቶች ላይ የሚፈጠሩትን ተጽዕኖ በማስገንዘብ እንዲወገዱ በማድረግ፣ ወጣቶች በውሳኔ ሰጪነት እኩል እንዲሳተፉ ማድረግ።

  • ወጣቶች የፈጠራ ዝንባሌያቸው እንዲጎለብት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የሥራ ባህላቸው ዳብሮ ሥራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውንና ሀገራቸውን ከድህነት በማውጣት የሚታገሉ እንዲሆኑ ማድረግ።

  • ወጣቶች ኅብረ ብሄራዊ አንድነታቸውን በመጠበቅ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል በማጎልበት፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል።

የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ መርሆዎች

  • ህዝባዊነት

  • ዳሞክራሲያዊነት

  • የህግ የበላይነት

  • ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት

  • ተግባራዊ እውነታ

  • ሀገራዊ አንድነትና ኅብረ-ብሄራዊነት

የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ እሴቶች

  • ህብረ-ብሄራዊ አንድነት

  • ወንድማማችነት / እህትማማችነት

  • የዜጎች ክብር እና እኩልነት

  • ነጻነት

  • መከባበር እና መቻቻል

  • እኩል ተሳትፎ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት

የሴቶች ክንፍ ዘርፍ

Miss Gete Bekele Debele

የሴቶች ክንፍ ዘርፍ ሀላፊ

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አላማዎች

  • የብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም በህዝቡ ውስጥ ሰርፆና ተግባራዊ ሆኖ መላው የአገራችን ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ።

  • ሴቶች በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ፣ በየደረጃው የልማት፣ የዲሞክራሲና የሰላም ግንባታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል።

  • ሴቶች ህገ-መንግስቱ ያጎናፀፋቸውን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በትክክል ሥራ ላይ እንዲውሉ፣ ጠንካራ አደረጃጀት በመፍጠር ለመብታቸው እንዲታገሉ ማስቻል።

  • የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የሴቶችን አቅም በመገንባት፣ የሴቶች እኩልነትን የሚገድቡ ባህላዊና ልማዳዊ ተጽዕኖዎችን በመለየት፣ ለሀገር እድገትና በሴቶች ላይ የሚፈጠሩትን ተጽዕኖ በማስገንዘብ እንዲወገዱ በማድረግ፣ ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት እኩል እንዲሳተፉ ማድረግ።

  • ሴቶች የፈጠራ ዝንባሌያቸው እንዲጎለብት፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ የሥራ ባህላቸው ዳብሮ ሥራ ፈጣሪ በመሆን እራሳቸውንና ሀገራቸውን ከድህነት ለማውጣት የሚታገሉ እንዲሆኑ ማድረግ።

  • ሴቶች ኅብረ-ብሄራዊ አንድነታቸውን በመጠበቅ፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህል በማጎልበት፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል።

የብልፅግና ሴቶች ክንፍ መርሆዎች

  • ህዝባዊነት

  • ዳሞክራሲያዊነት

  • የህግ የበላይነት

  • ልማትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት

  • ተግባራዊ እውነታ

  • ሀገራዊ አንድነትና ኅብረ-ብሄራዊነት

የብልፅግና ሴቶች ክንፍ እሴቶች

  • እህታማማችነት

  • መካባበር እና መቻቻል

  • ህብረ-ብሄራዊ አንድነት

  • የዜጎች ክብር እና የሥርዓት ፅታ እኩልነት

  • ነፃነት

  • እኩል ተሳትፎ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት

Inspection and Ethics Commission Department

Mr. Temesgen Bitew Seyum

Head of the Inspection and Ethics Commission

የኮሚሽኑ ተግባራትና ኃላፊነት

የፓርቲውን ህይወት መጠበቅ

  • የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል።

  • የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራትና የሥነ-ምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ ክትትል ማድረግ።

  • የፓርቲ ሥነ-ምግባርን ያሻሽል ሙስናን ለመዋጋት ጥረቶችን ማድረግና ማስተባበር።

  • የሥነ-ምግባር ጥሰቶችን መመርመር፣ ተገቢውን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ።

  • ከፓርቲው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልእኮ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ።

  • በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ፣ በፓርቲው ማኮ/ሥአኮ ሲጠየቅ አጣርቶ የውሳኔ ሀሳብ ሪፖርት ለማ/ኮሚቴ አቀርባል።

የፓርቲውን አባላት መብት መጠበቅ

  • የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶችና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል።

  • ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ይመረምራል፣ የእርምት የውሳኔ ሀሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደ አግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል።

  • ፓርቲው ርምጃ የተወሰደበት አባል/ዕጩ አቤቱታውን በየደረጃው ላለው የፓርቲ መዋቅር አቅርቦ ካልረካ፣ በየደረጃው ላለው ኮሚሽን ሊያቀርብ ይችላል።

የፓርቲውን ሀብቶች መቆጣጠር

  • የፓርቲው ገንዘብ፣ ንብረትና ሰነዶች በአግባቡ መጠበቃቸውን ቁጥጥር ያደርጋል።

  • የፓርቲው አባላት መዋጮ በወቅቱና በትክክል መሰብሰቡን ይቆጣጠራል።

የኮሚሽኑ የውስጥ አሠራሮች

  • ዝርዝር የሥነ-ምግባር፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል።

  • ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ-ሀሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል።

  • ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል።

  • ለፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽኑ አባላትን በ 2/3 ድምጽ ያግዳል።

  • ስለ ሥራው ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል።

  • የኮሚሽኑን የውስጥ የአሰራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል።

የፓርቲያችን ዋነኛ ዓላማ ኅብረ ብሔራዊነቱ የተጠበቀ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፥ የሃይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማኅበረሰብ ማለታችን ነው።

Must Read

©2026- All Right Reserved. Designed and Developed by Woreda Three Prosperity Party Office.