የጥምቀት በዓል አከባበርን በማስመልከት የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮችና የወረዳው አጠቃላይ አመራር በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበርን አስመልክቶ በቅድመ ዝግጅት ዙሪያ የከተማ ደጋፊ አመራር ወ/ሮ መሳይ መርሻ የክፍለ ከተማ ደጋፊ አመራሮች ወ/ሮ ሙሉእመቤት ስራብዙ እና አቶ ያዬራድ ዳምጤ እንድሁም የወረዳው አጠቃላይ አመራር በተገኘበት የውይይት መድረክ ተካሄደዋል።
የውይይት መድረኩን የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሲ/ር ግሩም ንጉሴ እና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ኤርሚያስ የመሩ ሲሆን መጪው ከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም በሚከበርበት ሁኔታና መደረግ ስላለበት ቅድሚያ ዝግጅት ሁኔታዎች ላይ ከአጠቃይ አመራሮች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን በዓሉ ሐይማኖታዊ ቱውፊቱን በጠበቀ መልኩ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር አመራሩ ተልዕኮ በበላይነት በመውሰድ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚኖርባቸው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በማሳሳብ ውይይቱ ተጠናቋል።
ለሚ ኩራ ወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት
ጥር 08/2018 ዓ.ም