በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት የ2018 የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማና ከአስሩም ወረዳዎች ከመጡ የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን አፈፃፀሙን ገምግሟል።
በዚህም በነበረው የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም 27,509 ፀጋዎችን በመለየት ለ19,112 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር፣ለ70,360 ወጣቶችና ሴቶች በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠቱ፣በስራ እድል ፈላጊ ወጣቶች ምዝገባ ከ25ሺ በላይ መመዝገቡ፣ለ20,242 ወጣቶችና ሴቶች የልል ስልጠና መስጠቱ፣ከምግብ ዋስትና ተጠቃሚዎች፣ከብድር ስርጭትና ማስመለስ አንፃር የተሠሩ ስራዎች በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም በበጎ ፍቃድ፣በሪፎርም፣አገልግሎትን ከማዘመን፣የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግና ተጠያቂነትን ከማስፈን አንፃር የተሠሩ ተግባራት በስፋት ቀርበዋል።
መድረኩን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ እና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ልመንህ ምህረቱ የስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት ቁልፍ ተግባር መሆኑን በማንሳት በቀሪ ጊዜያት ያሉ ዕቅድን ለማሳካት ፀጋዎችን አሟጦ መጠቀም ፣ ተግባራትን መገምገምና በውጤት ማጀብ ፣ አመራሩን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ማስገባትና የተጠያቂነት ስርዓትን ማስፈን ፣ ተግባራትን ወጥ በሆነ መልኩ አስተሳስሮ መምራት ፣ ስራዎችን መሬት አስነክቶ መምራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ምክትል የስራ እና ክህሎት ሜክትል ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛ ደመቀ በበኩላቸው የ2ኛ ሩብ ዓመት የስራ ዕድል ፈጠራ ከሚፈለገው አኳያ ቀሪ ስራዎች ያሉ በመሆኑ የተግባሩን ክብደት በመረዳት መደበኛ ስራዎችን ከንቅናቄ ስራዎች ጋር አስተሳስሮ መስራት ፣ ተልዕኮ ተቀብሎ መፈፀም፣ ግምገማዎችን ወደ ውጤት መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በመጨረሻም በነበረው የስድስት ወር አፈፃፀም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቷል።











